በኢትዮጵያ በአንድ አመት ውስጥ ከአራት ሺ በላይ ዜጎች በተሽከርካሪ አደጋ ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የትራንስፖርት ሚንስቴር ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርቱ አስታወቀ።

ጥር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት ውስጥ 2008 ዓ.ም ብቻ በመላው ኢትዮጵያ ባጋጠመ ከተሽከርካሪ ጋር ተዛማጅ በሆኑ በደረሱ አደጋዎች በድምሩ 4 ሽህ ዜጎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከ10 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት አጋጥሟቸዋል።
ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የትራፊክ አደጋ ከዓመት ወደ ዓመት እየተባባሰ መምጣቱን እና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገራት ጥቂት ተሽከርካሪዎች ይላት አገር ስት ሆን በትራፊክ አደጋ ጉዳት ግን በአፍሪካ በቀድሚነት ተርታ ትገኛለች።