መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሃሰት የትምህርት ማስረጃ ይዘው ከሚሰሩት መካከል ደግሞ መምህራንና የጤና ባለሙያዎች መገኘታቸው በትውልዱ ላይ ከፍተኛ አደጋ መደቀኑን ዜጎች ይናገራሉ። በዲግሪ የተመረቁ መምህራን 8ኛ ክፍል ማስተማር አንችልንም ብለው ወደ አንደኛ ደረጃ እንዲመደቡ የጠየቁ መኖራቸውን የክልሉ ሌላው ባለስልጣን ይናገራሉ ። ህክምና ተምረው ሃኪም ያዘዘውን መድሃኒት በትክክል ለመስጠት የማይችሉ ፋርማሲስቶች መኖራቸውንም ባለስልጣኖች ይገልጻሉ ።
በኢትዮጵያ በርካታ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን በገንዘብ እንደሚገዙ ቀደም ብለው የወጡ የምርምራ ስራዎች ያመለክታሉ።
ችግሩ ከላይ እስከታች የተያያዘ በመሆኑ በቀላሉ ለመፍታት እንደማይችል አስተያየታቸውን የሰጡ እነዚሁ አመራሮች ይገላጻሉ። ከላይ እስከታች ይፈተሽ ቢባል ብዙ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ።