ሰኔ ፲፱ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የአይ.ኤም.ኤፍ እና የኢኮኖሚስት ዌብ ሳይቶች መታገዳቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጡ።
ምንጮቻችን እንደጠቆሙት ካለፉት ሁለት ቀናት ወዲህ የገንዘብ ተቋሙን እና የ ኢኮኖሚስት ድረ-ገፆችን ለማየት አልቻሉም።
ዓለማቀፉ የገንዘብ ተቋም( አይ.ኤም.ኤፍ) ሰሞኑን ኢት ዮጵያን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ የመንግስት ባለስልጣናት ኢኮኖሚው 11 በመቶ እንዳደገ የሚሰጡት መግለጫ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው ከማለቱም ባሻገር በተያዘው ዓመት የ ኢት ጵያ ኢኮኖሚ ያሳየው ዕድገት 5 በመቶ ብቻ ነው ማለቱ ይታወቃል።
የእድገት አሀዙን በተመለከተ በታየው የሰፋ ልዩነት ምክንያት፤ በኢትዮጵያ መንግስት ባለሥልጣናት እና -ከሳምንት በፊት ወደ ኢትዮጵያ አቅንተው በነበሩት በአይ.ኤም.ኤፍ ልኡካን መካከል ጠንከር ያለ ጭቅጭቅ እና ክርክር ተፈጥሮ እንደነበር መዘገቡ አይዘነጋም።
ይሁንና ሰሞኑን የገንዘብ ተቋሙ ዌብሳይት በኢትዮጵያ የታገደው ከዚህ ጋር በተያያዘ ይሁን አይሁን እስካሁን የተረጋገጠ ነገር የለም።
ከአይ ኤም ኤፍ በተጨማሪም የኢኮኖሚስትም ድረ-ገጽ በተመሣሳይ ታግዷል።
ኢኮኖሚስት በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢት ዮጵያ “አስመዝግቤዋለሁ” በምትለው ኢኮኖሚ ዙሪያ ጠጣር ትችቶችን ሲያቀርብ ቆይቷል።
የዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅትን ( ሲ.ፒ.ጄ)፣ የሂዩማን ራይትስ ዎችን እና የ ቪ.ኦ.ኤን ጨምሮ ከ 150 በላይ የሚሆኑ የተለያዩ ተቋማት ድረ-ገፆችና ብሎጎች በኢትዮጵያ እንዳይታዩ ከታገዱ ረዥም ጊዜ ማስቆጠራቸው ይታወቃል።
ይህን ሁሉ በማገድ ያልረካው የአቶ መለስ መንግስት ሰሞኑን ባወጣው አዲስ ህግ ደግሞ፤ በስካይፒ፣በጎግል ቶክ እና በያሁ መሴንጄር የድምፅ መልዕክት መለዋወጥ፦ ከ 10 እስከ 20 ዓመት በሚደርስ እስራት እንደሚያስቀጣ ደንግጓል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide