(ኢሳት ዜና – ሐምሌ 4/2009) እንደ አለማቀፉ የጤና ድርጅት በአውሮፓውያኑ 2012 ጥናት ከሆነ ወደ 61 ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በካንሰር ህመም ተይዘዋል።
እንደ ጥናቱ ከሆነ ኢትዮጵያውያኑ የተጠቁበት የካንሰር አይነት ደግሞ በህክምናው አለም በቀላሉ መከላከል የማይቻልና በፍጥነት የሚባዛ መሆኑን አመልከቷል።
ምናልባትም ችግሩን የከፋ እንዲሆን ያደረገው አንድ መቶ የሚሆን የተለያየ ባህሪ ያላቸው የካንሰር ሴሎችን የያዘ መሆኑ ነው ብሏል ጥናቱ።
በኢትዮጵያ የቤተሰብ መምሪያ ስፔሻላይዝድ ነርስ የሆኑት ሲስትር ሰናይት ላቀ አባባል ከሆነ በሀገሪቱ የካንሰር ህሙማን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨረ መቷል።
እንደ አውሮፓውያኑ በ2015 በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተደረገው ጥናት እንዳመለከተው ባለፉት ባለፉት 16 አመታት በካንሰር የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አሻቅቧል።
በተለይ በማህጸንና በጡት አካባቢ የሚከሰተው የካንሰር አይነት ቁጥሩ ከፍ ያለ ነው ብሏል።
ይህንን ችግር ለመቅረፍ ደግሞ በሀገሪቱ ለጉዳዩ እየተሰጠ ያልውን ዝቅተኛ ግምት ማሻሻል፣የመሳሪያዎችን ቁጥር መጨምርና ለሴቶች ጤና ክብካቤ ትኲረት ማድረግ ይገባል ብለዋል ሲስትር ሰናይት ላቀ።
እንደ አለም አቀፉ የጤና ተቋም መረጃ ከሆነ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጥር በ2015 ብቻ ከካንሰር ህመም ጋር በተያያዝ 8 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአለም ላይ ከሚሞቱ ስድስት ሰዎች አንዱ ህይወቱን የሚያጣው ከዚሁ ችግር ችግር ጋር በተያያዘ መሆኑን በምጠቆም ።
በአውሮፓውያኑ 2010 ብቻ ከካንስር ሀከማና ጋር በተያያዘ የተምደበው በጀት አንድ ነጥብ አምስት ትሪሊየን የአሜሪካን ዶላር መሆኑን ኢየሩሳሌም ፖስት አምልክቷል።