በኢሬቻ በአል ላይ የተሰው ኢትዮጵያውያንን አላማ ከግብ እንደሚያደርሱ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ

መስከረም ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በኤሪቻ በአል ላይ ለተገደሉት ኢትዮጵያውያን ሀዘናቸውን ገልጸው ንቅናቄያቸው“ ወገኖቻችን የተሰውለትን የፍትህ፣ የነፃነትና የእኩልነት ዓላማ ከዳር እስከሚደርስ ድረስ እስከመጨረሻው የደም ጠብታ እንታገላለን ብለዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ዝግጅታችንን  በቶሎ አጠናቀን ሊደበቅ በማይችልበት ሁኔታ በግልጽ የምንወጣበት ቀን  ሩቅ እንዳልሆነ አረጋግጣለሁ ያሉ ሲሆን፣በወያኔ ስር ተጠርንፎ የሚገኘው የኢትዮጵያ ወታደር አሁንም በትንሽ በትንሹ እንደጀመረው በሰፊው ተንቀሳቅሶ ከሥርዓቱ ጋር ሳይሆን ከሕዝቡ ጎን እንዲቆም የምናደርገው ጥረትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም አክለዋል።

የህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴዎች ለያካባቢያቸው የሚሆንና በየጊዜው የሚቀያየር የትግል ስልትና፤በወያኔ/ኢህአዴግ ንብረቶች፤የአፈናና የመገናኛ መዋቅሮች፤ የገንዘብ ምንጮችና ባጠቃላይ በስርዓቱ ላይ የኢኮኖሚና የስነልቦና ጫና በሚፈጥሩ ኢላማዎች ላይ ማነጣጣር እንዳለባቸው መክረዋል፤፡