ጥቅምት ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለድርጅቱ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት የኢትዩጵ ያመንግስት ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰባቸውም በማለት እያቀረበ ያለውን ሪፖርት ነዋሪዎቹ አጥብቀው ተቃውመዋል።
87 ሰዎችን በእጃን ቀብረናል ያሉት ኗሪዎች ዜናው የተነገረው ጉዳት ከደረሰ ከሳምንት በኃላ ሲሆን እርዳታ የመጣውም ብዙ ነገረ ከወደመ ከስድስት ቀናት በሁዋል መሆኑ ችግሩን የከፋ አደርጎታል ሲሉ አመልክተዋል። በድርጊቱ እጅግ ማዘናቸውን የገለጹት ነዋሪዎች ተቆርቋሪ
መንግስት የለንም በሚል ወቀሳ አቅርበዋል። ችግሩ አሁንም አስከፊ በሆነ ሁኔታ መቀጠሉን በመግለጽ ቀይ መስቀል እንዲድረስላቸው ተማጽነዋል።
የአዋሽ ሙላትን በተመለከተ ኢሳት ከሁለት ቀን በፊት ባቀረበው ዘገባ ነዋሪዎች የሞቱ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ብለው መገመታቸውን ገልጾ ነበር።