መጋቢት 13: 2009)
በአዲስ አባባ በርካታ አካባቢዎች የውሃ እጥረት ችግር ተባብሶ መቀጠሉን ነዋሪዎች አስታወቁ።
የከተማዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ለከተማዋ የውሃ አቅርቦት የሚያገለግሉ ጉድጓዶች በመድረቃቸው ምክንያት የውሃ እጥረቱ መከሰቱን በቅርቡ መግለፁ ይታወሳል። ባለስልጣኑ የውሃ እጥረቱ ጊዜያዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ተደርጓል ሲል ከቀናት በፊት መግለጫን ቢሰጥም ነዋሪዎችና የተቋማት ባለቤቶች ችግሩ ዕልባት አለማግኘቱን ይገልጻሉ።
ለአመታት የቆየው የመዲናይቱ የውሃ እንዲሁም የመብራት እጥረት በዕለት ከእለት ኑሯቸው ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ የተናገሪቱ ነዋሪዎች ችግሩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናን እያሳደረባቸው መሆኑንም ተናግረዋል።