ኢሳት ዜና (ጥቅምት
በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ አሜሪካን ግቢ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ሶስት ሺ የሚጠጉ የንግድ ተቋማት ቦታው ለልማት ይፈለጋል ተብሎ ንብረታቸው መታሸጉን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጡ።
የንግድ ተቋማት መታሸግን ተከትሎም የአካባቢው ነዋሪዎች መሰረታዊ የፍጆታ እቅርቦቶችን ለማግኘት ተቸግረው እንደሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል።
ወፍጮ ቤቶች ሱቆችና ምግብ ቤቶች ከታሸጉበት የንግድ ተቋመት መካከል እንደሚገኙበት የተናገሩት ነዋሪዎች የመንግስት አካላት የወሰዱት እርምጃ ተገቢ አለመሆኑን አስታውቀዋል።
የንግድ ድርጅቶቻቸው ከመኖሪያ ቤታቸው ጋር ተያይዞ የነበሩት በርካታ ሰዎችም ማደሪያን አጥተው እንደሚገኙ ነዋሪዎቹ አክለው ገልጸዋል።
ወደ አካባቢው ምንም አይነት ተሽከርካሪ እንዳይዘዋወር እገዳ ተጥሎ የሚገኝ ሲሆን፣ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን የሚሰማላቸው አካል እንዳላገኙ ተናግረዋል።
ተክለ ሀይማኖት እና ጃሊያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከታሸጉት የንግድ የንግድ ተቋማት በተጨማሪ በርካታ መኖሪያ ቤቶችም ይነሳሉ መባሉ በነዋሪዎች ዘንድ ስጋትን ፈጥሮ እንደሚገኝ ታውቋል።