ህዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ለህዳሴው ግድብ ማሰሪያ ቃል ከተገባው ገንዘብ ውስጥ እስካሁን የተሰበሰበው አነስተኛ መሆኑ ታወቀ
ሙስሊሙ ኀብረተሰብ በትናንትናው ዕለት የታሰሩትን የሙስሊም ችግሮች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ለመጠየቅ ቃሊቲ
እስር ቤት ማጨናነቃቸውን የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡
ዜና 1
በአዲስ አበባ የሚፈርሱትን ቤቶች ተከትሎ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየተፈጸመ ነው ተባለ
ሰሞኑን ገርጂ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከ2 ሺ ያላነሱ ቤቶች መፍረሳቸውን ተከትሎ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦችና እና ታዛቢዎች ገልጸዋል።
ካለፈው አርብ ጀምሮ በቦሌ ቡልቡላ አካባቢ የሚኖሩትን ቤቶች ከቦሌ ክፍለከተማ፣ ከፌደራል ፖሊስ እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተውጣጣ አፍራሽ ግብረሀይል ቤቶችን ሲያስፈረስ መዋሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ቤቶች በሚፈርሱበት ጊዜ ፖሊሶች በአካባቢው ሰዎች ላይ ከፈጸሙት ድብደባ በተጨማሪ የመንግስትን ድርጊት የተቃወሙ 20 ወጣቶችን ይዘው አስረዋል። አንዲት ነፍሰጡር ደግሞ ቤቷ በላዩዋላይ ሲፈርስባት በመመልከቷ ራሱን ስታ መሞቷን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ልጆቻችንን ከጅብ ለመታደግ ቀይ መስቀልና የኢትዮጵያ ህዝብ ይድረሱልን ሲሉ ነዋሪዎች ተማጽነዋል ፡፡
ከሳምንት በፊት በላፍቶ ክፍለ ከተማ የፈረሱትን ቤቶች ተከትሎ አምስት ሰዎች መሞታቸውን መግለጻችን ይታወሳል።
መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም። የመንግስት እርምጃ በዚሁ ከቀጠለ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች መካከል ከአምስት እጁ አንዱ ቤት አልባ ሊሆን ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። በላፍቶ ክፍለከተማ ብቻ ከ30 ሺ ያላነሱ ቤቶች ይፈርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። በገርጂ የሚፈርሱት አጠቃላይ የቤቶች ቁጥር እስካሁን አልታወቀም።