በአዲስ አበባ ወላጆች ፌደራል ፖሊሶችን ምከሩልን ሲሉ ተናገሩ

መስከረም ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለተሞች የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ወላጆች ለስብሰባ እየተጠሩ ልጆቻቸውን እንደሚክሩ ተነግሮአቸዋል። በማህበራዊ ሚዲያ የሚደረገው ቅስቀሳ አገራችንን ለብጥብጥ እየዳረጋት በመሆኑ፣ ልጆቻችሁ ትምህርት ቤት በሚገቡበት ወቅት ረብሻ እንዳያስነሱና ማህበራዊ ሚዲያውን እንዳይከታተሉ ምከሩዋቸው ሲሉ ተናግረዋል።

በእዛኛው ወላጅ የሚጣ ለውጥ የለም በሚል ስብሰባውን አለመሳተፋቸውን የገለጹት ወላጆች መንግስት ለሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ የተነሱትን ችግሮች ሊፈታ ይገባል ብለዋል

አንድ ተሰብሳቢ ደግሞ ልጆቻችንን ምከሩ ትላላችሁ ይልቅ የልጆቻችንን ትምህርት ቤት የሚጠብቁትን የፌደራል ፖሊሶችን ምከሩልን ፣ እነሱ አማርኛ እንኳን የማይሰሙ በመሆናቸው ከልጆቻችን ጋር መግባባት አልቻሉም” በማለት ተናግረዋል

ስብሰባውን የሚመሩት ሹም ፌደራል ፖሊስ በጅምላ እርምጃ አይወስድም ብለው ሲመልሱ ህዝቡ በማጉረምረም መልሱን ሳይቀበለው ቀርቷል።

ሌላ ተሰታፊ ደግሞ ችግሩ የተፈጠረው ገና ማህበራዊ ሚዲያ ሳይፈጠር በመሆኑ ፣ ችግሩን በማህበራዊ ሚዲያ ከማሳበብ ትክክለኛውን መፍትሄ መፈለጉ ለሁሉም ይጠቅማል ብለዋል።