ግንቦት ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን ሀገር አቀፍ የሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የምክክር መድረከ ላይ የቀረበ ጥናት እንደሚያሳያው በአዲስ አበባ ቤተሰብ አልባ ለችግር የተጋለጡ ህፃናትን ይዘው የሚለምኑ እናቶች ቁጥር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። አብዛኞቹ እናቶች ከተለያዩ የአማራ ክልል ወረዳዎች የመጡ ናቸው።
አጥኝዎች እንደሚሉት በገጠር እየከፋ የመጣው ድህነት ፥ እናቶች ራሳቸውን ለማስተዳደር የሚችሉበትን አቅም ለመፍጠርና የእለት ጉርሳቸውን ለማግኘት ከፍተኛ ጫና ስለፈጠረባቸው አካባቢያቸውን ጥለው ለመስደድ ተገደዋል።
አብዛኞቹ እናቶች ከአማራ ክልል መምጣታቸው በክልሉ ያለው ድህነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መሄዱን የሚያሳይ ነው።