ኢሳት (ሃምሌ 1 ፥ 2008)
በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ከ10 ለሚበልጡ ነዋሪዎች ሞት ምክንያት የሆነውን ህገ-ወጥ የተባሉ የመኖሪያ አካባቢዎችን የማፍረሱ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር አርብ አስታወቀ።
የከተማዉ አስተዳደር ህገ-ወጥ ናቸው ያላቸዉን የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ለማፈርስ ባካሄደዉ ዘመቻ 95 በመቶ የሚሆኑት በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ከሁለት በላይ በህገ-ውጥ መንገድ መሬት የወረሩ መሆኑን ገልጿል።
በኣዲሰ አበባ ከተማ በተለያዩ ስፍራዎች ሊካሄድ የታሰበው የማፈረስ ዘመቻ በቀጣዩ ወራት ተጠናክሮ አንደሚቀጥል የከተማዋ አስተዳደር አርብ ባካሄደዉ ጉባዔ ውሳኔ ማስተላለፉን የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ዘግብዋል።
የከተማዉ አስተዳደር በቅርቡ በላፍቶ ክፍለ-ከተማ ባካሄደዉ ህገ-ውጥ የተባሉ የመኖሪያ ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ በነዋሪዎች ዘንድ ተቃዉሞ ቀስቅሶ በትንሹ ስድስት ሰዎች መገደላቸዉ ይታወቃል።
የኣዲሰ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ሁለት የፖሊስ አባላትና አንድ የወረዳ ስራ አስፈጻሚ ማንነታቸዉ ባለታወቀ አካላት ግድያ አንደተፈፀመባቸዉ ያስታወቀ ሲሆን፣ የፅጥታ ሀይሎች በአከባቢዉ በወስዱት አርምጃ በትንሹ አራት ሰዎች መገደላችውን እማኞች ይገልፃሉ።
ከወራት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በቦሌ ክፍለ ከተማ ተካሂዶ በነበረዉ የቤት ማፈረስ ዘመቻ ግጭት ተከስቶ ከ10 የሚበልጡ ሰዎች መገደላችዉ ይታወቃል።
በከተማዋ አየተካሄደ ያለዉን ዘመቻ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት ቢሆንም የኣዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘመቻዉ ተጠናክሮ አንደሚቀጥል አስታውቋል።
በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 10 አና 11 አከባቢ ተጨማሪ ህገ-ውጥ የተባሉ የመኖሪያ ቤቶችን አንደሚፈርሱ አስተዳደሩ ሲገለፅ የቆየ ሲሆን በሌሎች የከተማዋ ስፍራዎች ይፈርሳሉ በተባሉ መንደሮች ውይይት ሲካሄደ መቆየቱን ለመረዳት ተችሏል።
የከተማዉ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ዙሪያ በፈረሱ የመኖሪያ ቤቶች አከባቢ የጎልፍ መጫወቻን ጨምሮ በርካታ የልማት ፐሮጀግቶቸ ተግባራዊ አንደሚደረጉ ይገልፃል።
ኣዲሰ አበባ ከተማን ወደ ኦሮሚያ ክልል ለማስፋፋት ፀድቆ የነበረው አቅድ በበርካታ ነዋሪዎች ዘንድ ተቃዉሞን ቀስቅሶ ወደ 400 የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸዉን ሂዩማን ራይት ዎች በቅርቡ ይፋ ማድረጉን የሚታወቅ ነዉ።