በአዲስ አበባ ሃና ማርያም እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተፈናቀሉ ዜጎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

በአዲስ አበባ ሃና ማርያም እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተፈናቀሉ ዜጎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) ቤታቸው የፈረሰባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የሃና ማርያም አካባቢ ነዋሪዎች በድጋሜ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ መስተዳደር ባለስልጣናት ለተፈናቃዮች መልስ እንደሚሰጡ ቃል ቢገቡም ነዋሪዎቹን ግን የሚያረካ ሊሆን አልቻለም። የመስተዳድሩ አመራሮች መልስ ያላረካቸው ተፈናቃዮች፣ ጥያቄያቸውን በድጋሜ ለጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ለማቅረብ ወደ ቤተመንግስት ቢያቀኑም መሃል ላይ በፌደራል ፖሊስ እንዲበተኑ መደረጉን ያነጋገርናቸው ሰዎች ተናግረዋል።