ሚያዚያ ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሜልበርን ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የበላይ አስተዳዳሪ እና እንዲሁም የአውስትራሊያ ሐገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ሆነውለበርካታ አመታት ሲያገለግሉ የነበሩት ሊቀ ካህናት መዘምር ብሩ በድንገት በተወለዱ በ71አመታቸው አፕሪል 18/ 2016 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል::
ሊቀ ካህናት መዘምር ብሩ ከልጅነታቸው ጀምሮ በቤተ/ክ ድጓ ጾመ ድጓንና አቋቋም በታወቁ የጎንደር ጉባዕዎች፣ ቅኔን በጎጃም እንዲሁም ዘመናዊ ትምህርትም በሩሲያ የተማሩ ታላቅ ሊቅ እንደነበሩ የሚያውቁዋቸው ይናገራሉ።
ሊቀ ካህናት መዘምር ብሩ በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል በማለት አስተዋጽኦ በማድረግ ይታወቃሉ። በተለይም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዢን ኢሳትን በግል ገንዘባቸው በመደገፍም ሆነ የመዳሃኒአለም ምእመናን ኢሳትን እንዲደግፉ በማበረታታት የሚታወቁ ታላቅ አባት ነበሩ ሲሉ በአውስትራሊያ የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ ሊቀመንበር ወ/ሮ ሃና ለገሰ ገልጸዋል። በሃገራችን የከተሰተውን ረሃብ አስመልክቶ ክርስትያኑ ማህበረሰብ ወገኖቹን እንዲያስብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደነበሩም ወ/ሮ ሃና ገልጸዋል።
የቀብር ስነ ስርአታቸው የሚፈጸመው ቅዳሜ አፕሪል 23/2016) ጠዋት በሜልበርም ደብረ ሰላም መድኃኔአለም ቤተክርስቲያን የፍትሓተ ፀሎት ከተደረገ በኋላ ከቀኑ1:00pm
በ:-Keilor Cemetery
Cemetery Rd & Ely Ct,
Keilor East VIC 3033 ነው።