በአዋሳ የታሰሩ የአንድነት አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ሰኔ ፲፯(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ያለፍቃድ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ህገወጥ ቅስቀሳ አድርጋችሁዋላ በሚል የታሰሩት የአንድነት አመራሮች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የ5 ሺ ብር ዋስትና እንዲያስይዙ እና እንዲፈቱ ተጠይቀዋል።

የቀጠሮ ጊዜያቸው የፊታችን አርብ ቢሆንም፣ እስረኞቹ ያለቀጠሮ እንዲቀርቡ ተደርጎ ያዋስትና መብት ተፈቅዶላቸዋል። ባለፈው ሰኞ ችሎቱ የእስረኞችን የዋስትና መብት ከልክሎ ነበር።

የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ባለፈው እሁድ በአዋሳ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ በመታሰራቸው ሰልፉ ሳይካሄድ መቅረቱን መዘገባችን ይታወሳል።

ዋስትና የተጠየቁት አመራሮች የዋስትና ገንዘብ ለማስያዝ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖች ለኢሳት ገልጸዋል።

ፓርቲው በደቡብ ክልል የሚታየውን አፈና የሚያወግዝ ጠንካራ መግለጫ አውጥቷል።