በአዋሳ ከተማ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው

ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ባለፉት 2 ሰማንታት በአዋሳ የነበረው ውጥረት እየተባባሰ በመምጣት ላይ ሲሆን፣ ትናንት ማታ በፌደራል ፖሊስና በህዝቡ መካከል በተነሳ ግጭት 1 ሰው ሲገደል ሁለት ደግሞ ቆስለዋል።

ግጭቱ የተነሳው በአዋሳ ከተማ ወልደአማኑኤል ዱባለ አደባባይ አካባቢ የተካሄደውን የሰርግ ስነስርአት ተከትሎ ነው። የሲዳማ ወጣቶች በሲዳምኛ እየጨፈሩ ሙሽሮችን ለመቀበል ሲሄዱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ተኩስ ከፍተውባቸዋል። በፖሊሶች ድርጊት የተበሳጩት የከተማዋ ነዋሪዎችም በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ድንጋዮችን በመወርውር ተቃውመዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላትም ተቃውሞን ለመበትን በርካታ ጥይቶችን ሲተኩሱ አድረዋል።

በዛሬው እለትም በአንዳንድ አካባቢዎች የተኩስ ድምጽ ይሰማ ነበር። ከባድ መሳሪያዎችን የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን አጨናንቀው መዋላቻውን፣ ውጥረቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱንና በማንኛው ጊዜ የከፋ ግጭት ሊነሳ እንደሚችል በስፍራው የሚገኘው ዘጋቢያችን ገልጧል።

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣  የግብርና ሰራተኞች፣ መምህራን፣ የክልሉ ፖሊስ ተወካዮች፣ የምክር ቤት አባላትና  እና ሌሎችም ከ 300 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ባለፈው ቅዳሜ በአዋሳ ከተማ በህቡእ ተሰባስበው የሲዳማ ወጣቶች ንቅናቄ የሚል ድርጅት መመስረታቸውን መግለጣችን ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide