በአብድራፊ ከተማ በትግራይ ልዩ ሃይል አባላትና በነዋሪዎች መካከል ከፍተኛ የተኩስ ልውጥጥ እየተካሄደ ነው

ነሃሴ  ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአብድራፊ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ባለሀብቱ አቶ ታያቸው  በአብድራፊና አብርሃ ጅራ መሃል ኮረደም ቴሌ በሚባል  ቦታ ላይ በትግራይ ክልል ልዩ አባላት መደገላቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ግጭት ተፈጥሮአል። በፓትሮል መኪና የመጡ ወታደሮች አቶ ታያቸውን ከመኪና አውርደው ከደሉዋቸው በሁዋላ፣ ተመሳሳይ ተልእኮ ይዘው በመምጣት አቶ በርጃለው የተባሉ የልዩ ሃይል አባልን ገድለዋቸው አምልጠዋል። በእርምጃው የተበሳጨው የአካባቢው ህዝብ የጦር መሳሪያውን በመያዝ ገዳዮችን ተከታትሎ ጫካ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓል። ወታደሮቹም ከጫካ ሆነው ከአካባቢው ህዝብ ጋር የተታኮሱ ሲሆን፣ አቶ ኪሮስ የሚባል ሰው በተኩሱ ልውጥ መሃል ተገድለዋል።

አቶ በርጃለው  በአብርሃ ጅራ ነዋሪ የሆኑ የልዩ ሃይል አባል  ቢሆኑም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሳቸውን ከህዝብ ጎን በማሳለፍ አገዛዙን ሲቃወሙ ቆይተዋል። በዚህም የተነሳ በህወሃት የደህንነት አባላት ራዳር ውስጥ ገብተው ቆይተዋል። ይህን ዜና እስካጠናከርንበት በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 11 ሰአት ድረስ የተኩስ ልውውጡ ሲካሄድ ቆይቷል።