ህዳር 5 (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ለአስር ቀናት በሽቦ ታስራ በአሰሪዋ ስትደበደብ የቆየችው ኢትዮጲያዊ የቤት ሰራተኛ ስቃዩማ መከራው በዝቶባት ግርፋትና ጭካኔው ጠንክሮባት በታሰረችበት መሞቷን የተመለከተው ያሰሪዋ ልጅ ለፕሊስ ጥቆማ መስጠቱና ሞቷ መታወቁን ዘገባው አመልክቷል።
የአቡዳቢ ፍርድ ቤትን ዋቢ ያደረገው ይህ ዘገባ ጉዳዩ ፍ/ቤት ቀርባ ኢትዩጲያዊቷን ሰራተኛ አስራ መግረፏን ያመነች ሲሆን የፈላ ሲሆን የፈላ ውሃ እላዩ ላይ መድፋቷን ግን ክዳለች።
ለፖሊስ ቃላቸውን የሰጡትን የሰጡት የገዳዩ ልጆች እናታቸው ሰራተኛዋን ኢትዮጲያዊ በየቀኑ ታሰቃያትና ትገርፋት እንደነበር ተናግረዋል።
ለፍርድ ቤቱ የቀረበ የሃኪም ማሰረጃ እንዳመለከተው የኢትዮጲያዊቷ ሞት በደረሰባት ከፍተኛ ድብደባ በአጠቃላይ በሰውነቷ ላይ ያስከተለው ቁሰለት መመርቀዝ በማስከተሉ መሆኑን ከማብራራቱ በላይ በአይኗ ላይ የደረሰ ድብደባም አይኗ ውስጥ መድማትን ማስከተሉን አመልክቷል።
ኢትዮጲያዊቷ የቤት ሰራተኛ ሰነፍ በመሆኗ ደበደብኳት የምትለው ተከሳሽ ሆን ብዬ ለመግደል ያደረኩት አልነበረም ስትል ልፍርድ ቤቱ ገልጻለች።
የሟች ኢትዮጲያዊ ተከላካይ ጠበቃ ልጆቹ መጥተው የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ፍ/ቤት ለጠየቀው ጥያቄ የገዳዩ አውንታና እንቢታ ባይሰማም ጠበቃው ለፖሊስ የሰጡት ምስክርነት በቂ መሆኑን በመግለጽ እንደማይፈልጓቸው ገልፀዋል።