(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 20/2011)በአሶሳ ዩኒቨርስቲ ያለው ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ መሆኑን የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ገለጹ።
ዘርን መሰረት ያደረገ በሚመስለው ግጭጥ አሁንም በተማሪዎች መካከል መከፋፈልና ድንበርን አስቀምጡ የማስፈራራቱ ሒደት መቀጠሉንም ተማሪዎቹ ይናገራሉ።
እንደተማሪዎቹ ገለጻ ከሆነ በዩኒቨርስቲው ተመድበው ከነበሩት አብዛኞቹ ተማሪዎች ወደ መጡበት ተመልሰዋል።–አሁን ያሉትም ቢሆኑ መሄጃ ትራንስፖርት እየተጠባበቁ መሆኑን ይናገራሉ።
በግቢው ውስጥ ያሉት ተማሪዎችም ቢሆኑ በዩኒቨርስቲው ይውላሉ እንጂ አዳራቸው ግን ሌላ ቦታ ነው።
ይህ ባለበትና ሁኔታዎች አስፈሪ በሆኑበት ሁኔታ ውስጥ የዩኒቨስርቲው አስተዳደር ሰኞ ትምህርት እንደሚጀመር አስታውቋል ብለዋል።
በዩኒቨርስቲው የተለያዩ ምክክሮች ከተደረጉ በኋላ ግጭቱ ረግቦ ወደ ሰላም ተመቷል የሚሉ መረጃዎች ይሰራጩ እንጂ መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን የተለየ ነው ይላሉ።