በአሶሳ ብሄርን ማእከል ባደረገ ጥቃት 3 ሰዎች ተገደሉ

በአሶሳ ብሄርን ማእከል ባደረገ ጥቃት 3 ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከሳምንት በፊት በስልጣን ላይ የነበሩ የህወሃት አባላት በብሄር ብሄረሰቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ በርታና ጉምዞች በአማራ እና ኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም አስደርገው 3 ሰዎች መሞታቸውንና ከ20 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
የህወሃት ሰዎች በአካባቢው እንደነበሩ እና ባምባሲና እና አሶሳ ዙሪያ እየዞሩ የበርታ ልጆቹን ሲቀሰቅሱ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃቱ ትናንት እንዲፈጸም የተደረገው ዛሬ ለዶ/ር አብይ የተጠራውን የድጋፍ ሰልፍ ለማደናቀፍ እንደበር እነዚሁ ምንጮች ገልጸዋል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የተወሰነ ጉዳት እንደደረሰበት፣ የተወሰኑ ባጃጅ መኪናዎች እንደተሰባበሩና እስከ 3 ሰኣት ድረስ ወደ አዲስ አበባና ሌሎችም አካባቢዎች የሚካሄደው የትራንስፖርት ፍሰት ተቋርጦ እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል።
አሁንም በአካባቢው ውጥረት እንዳለ ታውቋል።