ኢሳት (መስከረም 24 ፥ 2009)
በኦሮሚያ ክልል ዕሁድ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ማክሰኞ ሶስተኛ ቀን በአርሲ እና በቦረና ዞን ስር በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ተባብሱ መቀጠሉን እማኞች ለኢሳት ገለጹ።
በቡሌ ሆራ ማክሰኞ ጠዋት በነዋሪዎችና የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በትንሹ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉንና የወረዳው ፖሊስ ጣቢያ በተቃውሞ ምክንያት መውደሙን ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ነዋሪዎች አስረድተዋል።
ዕሁድ በቢሾፍቱ ከተማ የደረሰውን የበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት በማድረግ በክልሉ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ለሶስተኛ ቀን በአዳዲስ አካባቢዎች ሁሉ በመሰራጨት ላይ መሆኑን ከሃገር ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
በቡሌ ሆራ እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ ተቃውሞ ለሶስተኛ ቀን በአዳዲስ አካባቢዎች ሁሉ በመሰራጨት ላይ መሆኑን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
በቡሌ ሆራ እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ ተቃውሞ ነዋሪዎች በወሰዱት ዕርምጃ በወረዳው አንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት መሳሪያ ጭምር መዘረፉን እማኞች ገልጸዋል።
በትንሹ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን የተናገሩት ዕማኞች ቁጣ ያደረባቸው ነዋሪዎች በወረዳው የሚገኝ የኢህአዴግ ጽ/ቤትን ጭምር እንዳወደሙና አድማ በታች ወታደሮችን በቁጥር ልቀው በመገኘው ትጥቃቸውን ወስደው ከስፍራው እንዳባረሯቸው ከኢሳት ጋር ቃለምልልስን ያደረጉት እማኞች አስረደተዋል።
በምስራቅ አርሲ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ እና የተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ለሶስተኛ ቀን በቀጠለው ህዝባዊ ተቃውሞ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ድርጊቱን ለመቆጣጠር የሃይል ዕርምጃ እየወሰዱ መሆኑም ተነግሯል።
ይሁንና በሰው ህይወት ላይ ስለደረሰው አደጋ የተለያዩ መረጃዎችን በመውጣት ላይ ሲሆኑ ቁጥሮቹን ከገለልተኛ አካል ማጣራት አልተቻለም።
የኦሮሚያ ክልል ተቃውሞን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ መሆኑን ማክሰኞ ምሽት ገልጿል።