ሐምሌ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሻለቃ ማእረግ ያለው ፖሊስ አዛዥ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቹ ላይ በጩቤ ተወግቶ መገደሉን የደረሰን ዜና ያመለክታል። ግድያውን ተከትሎ ፖሊስ በትናንትናው እለት እና ዛሬ ከፍተኛ ፍተሻ ሲያካሂድ ውሎአል።
የገዳዮቹ ማንነት እስካሁን አልታወቀም። በዛሬው እለት በሻሸመኔ ከወትሮው በተለየ ቁጥር በየቦታው ፍተሻ ሲያኪዱ የታዩት የፌደራል ፖሊሶች፣ ምናልባትም ግድያውን ከሙስሊሞች ጥያቄ ጋር ሊያያይዙት እንደሚችሉ ፍንጮች መታየት መጀመራቸውን ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖች ለኢሳት ገልጸዋል።