በአማራ ክልል የበርበሬና የምስር ዋጋ ከእጥፍ በላይ ጨመረ

ሐምሌ ፲፮ (አስራስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ በሚገኙ በሁሉም አካባቢዎች 38 ብር ይሸጥ የነበረው አንድ ኪሎ በርበሬ ፣ 185 ብር በመሸጥ ላይ ሲሆን፣ 26 ብር በኪሎ ይሸጥ የነበረው ምስር ደግሞ ከ50 ብር በላይ እየተሸጠ ነው። በተፈጠረው የዋጋ ንረት የክልሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው። ክልሉ በበልግ ወራት የተጠበቀው የምስር ምርት ባለመገኘቱ የተፈጠረ ነው ሲል፣ የበርበሬ እጥረት ማጋጠሙንም አልሸሸገም።
በዚህ ወር በመላ አገሪቱ የምግብ እህል ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ማእከላዊ ስታትስቲክስ መስሪያ ቤት ያወጣው መረጃ ያሳያል። በአንጻራዊ መልኩ ጋብ ብሎ የነበረው የዋጋ ንረት ተመልሶ ወደ ሰማይ እየወጣ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።