በአለም ላይ እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ የተሰቃየ የለም ያሉት አቶ ስብሀት ነጋ ዛሬ ያ ሁኔታ መቀየሩን ገለጡ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- አንዱ ጠግቦ ሲያድር ያልጠገበው ደግሞ በሰላም ተኝቶ ያድራል ብለዋል::

አዲስ አበባ ለሚታተመው ኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ከቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ በፊት የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህውሀት) መሪ የነበሩትና ዛሬ በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ ተጽዕኖቸው እየበረታ መሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ስብሀት ነጋ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህመም ወዲህ ሚዲያ ላይ በብዛት እየቀረቡ መገኘታቸውን በዚህም ለኢሳት ጭምር ቃለ ምልልስ የሰጡበትን ሁኔታን አስታውሰዋል::

“ከመለስ መታመም ጀምሮ ሚዲያውን ለምን አበዛህው ካልሆነ በቀር እኔ ከሚዲያ አልተለየሁም ፣ ፓል ቶክ የሚባል አለ ፣ በቪ ኦ ኤም ተሳትፌለሁ፣ ለኢሳት እንኮን ቃለ ምልልስ ሰጥቻለሁ፣ ለውለውልኝ ቃለምልልስ ሰጥቻለሁ” ብለዋል::

ከአቶ መለስ ማለፍ በሆላ ተጽዕኖቸው እየበረታ ስለመምጣቱ ለተነሳላቸው ጥያቄ ማስተባበያ የሰጡት አቶ ስብሀት ነጋ አቶ ሀ/ማሪያም ደሳለኝን ካገኞቸው ሁለት አመት እንዳለፋቸው ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳን  አጭር ይሁኑ ረዥም ጨርሰው እንደማያውቆቸው አብራርተዋል::

እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ በአለም የተሰቃየ ህዝብ ያለ አይመስለኝም፣ ይፈጠራል፣ ራቁቱን ይሞታል፣ ከተፈለገም ይገደላል” በማለት መናገራቸውን ተከትሎ ዛሬ ይህ ቀርቶል ወይ ተብለው የተጠየቁት  አቶ ስብሀት አሁን ያመጸ ህዝብ የለም፣ ተወልዶ ወደ ውትድርና ሂድ የሚል የለም ፣ ቀይ ሽብር የለም ፣ አንድ ዩኒቨርሲቲ ነበረን አሁን 32 ዩኒቨርሲቲ አለን ፣ አንዱ ጠግቦ ያድራል ባይጠግብም ተኝቶ ያድራል በማልት ምላሽ ሰጥተዋል:፡ ዛሬ የሚያለቅሱት ወላጅ አልባ የሆኑት የአፄ ሀይለስላሴ ስርአት ናፋቂዎች ፣ ኢሰፓዎች ፣ ኢህአታ እና መኤሶኖች ናቸው ሲሉ ፈርጀዋል::

በግምቦት 1981 በኮሌኔል መንግስቱ ሀ/ማርያም ላይ በተቃጣው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በሻቢያ በኩል ተባባሪነታችንን ተጠይቀው በህውሀት በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱን አስታውሰዋል::

” በ1981 ግንቦት ወር በመፈንቅለ መንግስት መንግስቱ ሀ/ማሪያምን ለመገልበጥ የሞከሩት፣ ሻቢያን ላኩብን፣ ልንገለብጠው ነው ብለው ፣ መንግስቱ በግል ቢገለበጥ ባይገለበጥ ስርአቱ ካልተለወጠ ብለን ትግላችንን ቀጠልን እንጂ አላገኘናቸውም:: በማለት ሻቢያ ጭምር ለመተባበር የፈቀደውን ሂደት ህውሀት አለመቀበሉን አብራርተዋል::

አቶ ሀ/ማሪያም ደሳለኝ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ችሎታ ያንሳቸዋል በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄ መለስም ከምክትሎቹ ከነ ተፈራ ዋልዋ፣ ከነ ዶ/ር ካሱ ኢላላ ነው ችሎታውን ያዳበረው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል::