ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያኑ ኦስሎ በሚገኘው የእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ገዢው ሃይል የወሰደውን እርምጃ ከማውገዝ በተጨማሪ የኢንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስላሉበት ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ባዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ አቶ አንዳርጋቸው የፍትህ ተምሳሌት፣ የነጻነት በር ከፋች ነው የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል።
ኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አቶ አንዳርጋቸው በግፍ የመን ውስጥ ተይዘው ወደ ኢትዮጵያ ከተላለፉበት ጊዜ ጀምሮ ተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎችን አድርገዋል።