መስከረም ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ እና በጋራ የምክክር መድረክ አዘጋጅነት በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ ላይ ሰፊ ህዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።
ውይይቱ በአገራችን የተቀጣጠለውን ህዝባዊ እምቢተኝነት የትግል ስልት ከመጨረሻው ግብ ለማድረስ የተያዘው የነጻነት ትግል ለውጤት እንዲበቃ ምን መደረግ አለበት የሚለውን አጀንዳ በመያዝ ሁሉም ለኢትዮጵያ ፍትህና ዲሞክራሲ መስፈን፣ ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከበሩ የሚሰሩ የፖለቲካ ድርጅቶችና ህዝባዊ ተቋማትና ግለሰቦች ሊያበረክቱት ስለሚገባ አስተዋጾ ውይይት አድርጓል።