በኖረዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ግንቦት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያኑ ተቃውሞውን ያዘጋጁት የኖርዌይ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ ያላገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመቃወም፣ እንዲሁም ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ ከደቡብ ሱዳን ተጠልፈው የተወሰዱትና የ8 አመታት ፍርድ የተፈረደባቸውን የአቶ ኦኬሎ አኳይን ጉዳይ ኖርዌይ እንዴት እየተከታተለችው እንደሆነ ለመጠየቅና በኢትዮጵያ የሚፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ለማጋለጥ መሆኑን የሰልፉ አስተባበሪ ከሆኑት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ፍቅሬ አሰፋ ገልጸዋል።
በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ዴስክ ሃላፊን ማነጋገራቸውንም አቶ ፍቅሬ ተናግረዋል