(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 19/2010)
እስላማዊ ታጣቂዎች በናይጄሪያ አንድ ት/ቤት በመውረር ከአንድ መቶ በላይ ሴት ተማሪዎችን አግተው ወሰዱ።የተማሪዎቹ ወላጆች የናይጄሪያ መንግስት ልጆቻቸውን በፍጥነት እንዲያስመልስ ጥሪ አቅረበዋል።ዕገታውን በተመለከተ ሃላፊነት የወሰደ ቡድን ባይኖርም ቦኮሃራም ድርጊቱን ሳይፈጽም አንዳልቀረ ታምኖበታል።
እስላማዊ ታጣቂዎች በናይጄሪያ አንድ ት/ቤት በመውረር ከአንድ መቶ በላይ ሴት ተማሪዎችን አግተው ወሰዱ፥የተማሪዎቹ ወላጆች የናይጄሪያ መንግስት ልጆቻቸውን በፍጥነት እንዲያስመልስ ጥሪ አቅረበዋል።ዕገታውን በተመለከተ ሃላፊነት የወሰደ ቡድን ባይኖርም ቦኮሃራም ድርጊቱን ሳይፈጽም አንዳልቀረ ታምኖበታል።
“ልጃችን ከታገተችበት ግዜ ጀምሮ እንቅልፍ በአይኔ አልዞረም፡አናቷም ለቅሶዋን ማቋረጥ አልቻለችም” በማለት ዛሬ ለናይጄሪያው ኒውስ ዴይ መግለጫ የሰጡት ከታጋቾቹ የአንዷአባት ናቸው።
የታጋቿ የ14 ዓመቷ አይሻ ካቻላ አባት ካቻላ ቡካር “ልጆቻችን ታጣቂዎቹ እጅ በቆዩ ቁጥር የሚከተለው ሁኔታ ያሳስበናል” ሲሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል።የናይጄሪያ መንግስትም ልጃገረዶቹን ልማስለቀቀ በፍጥነት እንዲንቀሳቀሰም ጥሪ አቅርበዋል፡
በናይጄሪያ በሰሜናዊ ምስራቅ ዩባ ግዛት ዳፓቺ በተባለውን ትምህርት ባለፈው ሳምንት የወረሩት ታጣቂዎች 110 ሴት ተማሪዎችን አግተው የወሰዱ ሲሆን፣የናይጄሪያ መንግስት ለቀናት በአየር ሃይል የታገዘ ዘመቻ ቢያደርግም የተገኘ ውጤት የለም።
የናይጄሪያ የማስታወቂያ ሚኒስትር ሚስተር ላይ ሞሃመድ በሰጡት መግለጫ የታገቱትን ሴቶች ለማግኘት የማንፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም በማለት ለሰለባዎቹ ቤተሰቦች መልዕክት አስተላለፈዋል።
ቦኮሃራም የተባለው አሸባሪ ቡድን በተደጋጋሚ በናይጄሪ ተማሪ ሴቶችን ሲያግት ቆይቷል።በተለይ የዛሬ አራት ዓመት እ/ኤ/አ በሚያዚያ 2014 276 ልጃገረድ ሴቶችን ያገተበት ድርጊት ዓለም አቀፍ መነጋገሪይ እንደነበርም የታወሳል።
እ/ኤ/አ በ 2002 የተመሰረተው ቦኮሃራም በምዕራብ አፍሪካ ሃገራት በናይጄሪያ ፣ኒጀር ፣ቻድ እና ሰሜን ካሜሩን ይንቀሳቀሳል።በአካባቢው እስላማዊ መንግስት ለመመስረት የሚንቀሳቀሰው ይህ ቡድን እስከ 9 ሺህ የሚገመቱ ታጣቂዎች እንዳሉትም ይነገራል።