(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 22/2010) በናይጄሪያ አንድ ነዳጅ የጫነ ተሽከርካሪ በእሳት ከመያያዙ ጋር በተያያዘ 9 ያህል ሰዎች መሞታቸው ተሰማ።
የተሽከርካሪውን ፍሬን መቆጣጠር ባለመቻሉ ተከሰተ በተባለው በዚህ አደጋ ሶስት የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችን ጨምሮ ከ50 በላይ ተሽከርካሪዎች በእሳት መጋየታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
የሃገሪቱ የመንገድ ደህንነት ተወካይ ለቢቢስ እንዳሉት ተሽከርካሪው ፍሬኑን መቆጣጠር ያቃተው በአካባቢው በሚገኝ ትልቅ ድልድይ አቅራቢያ ነው።
ትራፊክ በሚበዛበት አካባቢ መፈጠሩና ከተሽከርካሪው የፈሰሰው ነዳጅ አካባቢውን ሁሉ በማዳረሱ አደጋውን የከፋ አድርጎታል ብለዋል።
በአፍሪካ ግዙፍ የነዳጅ አምራች በምትባለው ናይጄሪያ የነዳጅ ፍንዳታ መከሰት ብዙም እንግዳ ነገር ባይሆንም የአሁኑ ፍንዳታ ግን የከፋና አደጋውም ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ነው ብሎታል ቢቢሲ በዘገባው።