በናይጄሪያ በተፈጸመ ጥቃት 45 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 29/2010) በናይጄሪያ ታጣቂዎች አደረሱት በተባለው ጥቃት 45 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ።

በሃገሪቱ ሰሜናዊ ግዛት ጉዋስካ በተባለችው መንደር ተፈጸመ የተባለው ይሄ ጥቃት ምክንያቱ ምን እንደሆነ አልታወቀም ብሏል ሮይተርስ በዘገባው።

በሃገሪቱ ቦኮ ሃራምን ጨምሮ ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች በናጄሪያ የተለያዩ መንደሮች ጥቃት ሲፈጽሙ ቆይተዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ በ2015 ተመርጠው ሃገሪቱን በመምራት ላይ ያሉት መሃመድ ቡሃሪም በሃገሪቱ ሰላምና ደህንነትን አስከብራለሁ ሲሉ ቃል ቢገቡም ያንን ማድረግ አልቻሉም በሚል ትችት እየተሰነዘረባቸው ነው።

የአሁኑ ጥቃት የሃገሪቱን የጸጥታ ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ አስገብቶታል ብሏል ዘጋባው።