ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለኢሳት ከስፍራው የደረሰው ዘገባ እንዳመለከተው ጋሻው የቆየ የተባለው የጸጥታ አስከባሪ የ28 አመቱን ጎሹ እያዩ የተባለውን አርሶ አደር ከመጠጥ ቤት ውስጥ እንዲወጣ ካደረገ በሁዋላ፣ ወደ እስር ቤት ወስዶታል።
በመንግስት የተሾመው ታጣቂ ወጣት የጸጥታ ማስጠበቅ ስራ ለመስራት በሚል ለመስክ ስራ ተልኮ በነበረበት ወቅት ነው ወጣቱን ያለምክንያት ወደ እስር ቤት ካስገባው በሁዋላ፣ ከእስር ቤት አስወጥቶ የገደለው።
ገዳዩ በቁጥጥር ስር ውሎ እንደተመሰከረበት የአካባቢው ሰዎች ገለጸዋል።