ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድንገተኛ ተቃውሞው የተካሄደው በመላ አገሪቱ ያለውን የሙስሊም ኢትዮጵያውያን የመብት ጥያቄን በሃይል መቆጣጠራቸውን የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያምንና አዲስ አበባ መስተዳድር የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ባስታወቁ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው። ዶ/ር ሽፈራው ሙስሊሙ በአደባባይ የሚያደርገውን ተቃውሞ ማቆሙንና ሌላ ስልት መጠቀም መጀመሩን ተናግረው ነበር።
ይሁን እንጅ ሙስሊሙ ከዚህ ቀደም ሲያደርገው እንደበረው ማስታወቂያዎችን በማህበራዊ ድረገጾች ሳያስታውቅ፣ ውስጥ ለውስጥ በተደረገ የመረጃ ልውውጥ በመሰባሰብ ተቃውሞ አሰምቷል።
ሙስሊሙ በፊኛዎች ላይ የተፃፉ መፈክሮችን ወደ ሰማይ ለቋል። “ትግሉ ይቀጥላል ሂጃብ መለያችን ኒቃብ ውበታችን ነው፣ ፍትህን ማዘግየት ፍትህን መንፈግ ነው” የሚሉ መፍክሮች ተጽፈው ተለቀዋል።