የካቲት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው ዓለማት ግጭት ባለባቸው አገራት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር ሆነው በሰላም አስከባሪን ከተሰማሩ አገራት ውስጥ ከፍተኛውን የሰራዊት ድርሻ ካሰማሩ አገራት ተርታ ኢትዮጵያ በቀዳሚነት ተሰልፋለች። ጥናቱ እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር በ2016 ዓ.ም በሰላም አስከባሪ ጦር የተሰማሩ አገራትን ዝርዝር ጥናታዊ አሃዝ አውጥቷል።
ኢትዮጵያ 8 ሽህ 326 ሰራዊት በማሰለፍ በቀዳሚነት ደረጃ ላይ ስትመደብ ባንጋላዲሽ በ8 ሽህ 274 ሁለተኛ፣ ሕንድ በ7 ሽህ 799 ሶስተኛ ደረጃን ስትይዝ ፓኪስታን 7 ሽህ 625 ሰራዊት በማሰለፍ በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።ይህም እነዚህ የአፍሪካና የኤሽያ አገራት ከአጠቃላይ 30 ከመቶ ሰራዊት አሰልፈዋል። በፀረ ሽብርና ሰላም አስከባሪነት የአውሮፓ ሕብረት አገራት በአጠቃላይ ከ6 በመቶ በላይ ድርሻ የላቸውም።
ጥናቱ ድሃ አገራት በደማቸው ሃብታሞቹ በገንዘባቸው እንደሚዘምቱ የፒው ሪሰርች ሴንተር ጥናታዊ ሪፖርት አመላክቷል።