የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የሚገኘው ደን ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ በእሳት እየወደመ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና የጸጥታ ሃይሎች እሳቱን ለማጥፋት በመረባረብ ላይ ናቸው። ይህን መረጃ እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ምን ያክል ስፋት ያለው ደን እንደወደመ ለማወቅ አልተቻለም።
በባሌ ዞን በወረዳ ሼዳ ቀበሌ አካባቢም ተመሳሳይ ቃጠሎ ተነስቶ በቁጥጥር ስር መዋሉን መንግስት አስታውቋል።