በተለያዩ ክልሎች ዜጎች በህገወጥ መንገድ መፈናቀላቸውን እየገለጹ ነው

ጥር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፋር ክልል በአሳይታ ወረዳ በርካታ ነዋሪዎች ከ40 አመታት ላናነሰ ጊዜ የኖሩባቸውን ቤቶች እንዲለቁ መታዘዛቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አብዛኞቹ ተፈናቃዮች በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል

በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ደግሞ ከ300 ያላነሱ ጉሊቶች ንብረታቸውን እየተቀሙ መደብሮቻቸው እንዲፈርስባቸው መደረጉ ታውቋል።ሰዎቹ ለረጅም ጊዜ ሲገለገሉበት የነበረውን ጉሊት እንዲያፈርሱ የተገደዱት ህገወጦች ናችሁ ተብለው ነው። ነዋሪዎች እቃችን እንድናንቀሳቅስ እድል ይሰጠን በማለት ቢጠይቁም የሚሰማቸው እንዳላገኙ ገለጽዋል፡ ኢሳት የክፍለ ከተማውን አመራሮች ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም።