(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 21/2010) በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ70 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።
በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል በሲዳማና ጋሞጎፋ 32 ሰዎች ሲሞቱ፣ በሶማሌ ክልል ደግሞ የ47 ሰዎች ህይወት ማለፉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በአካባቢዎቹ በጣለው የማያቋርጥ ዝናብ ምክንያት በደረሰ የመሬት መደርመስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ተገልጿል።
በሶማሌ ክልል ብቻ በጎርፍ አደጋ ወደ 200ሺህ የሚጠጋ ህዝብ መፈናቁሉም ታውቋል።
በስልጤ ዞንም 1ሺህ ነዋሪ በተመሳሳይ አደጋ ከ1ሺህ በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን ዓለማዓቀፉ የግጭት ዘጋቢ ኤጀንሲ ባወጣው ሪፖርት ላይ ተመልክቷል።