(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 21/2011)በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉራ ወረዳ ማንነትን መነሻ ያደረገ ጥቃት እንዳልቆመ ነዋሪዎች ገለጹ።
ባለፉት ሶስት ቀናት በቀስትና በተለያዩ የስለት መሳሪያዎች በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ኢሳት ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ጥቃቱ የአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ማነጣጠሩን የጠቀሱት ነዋሪዎች በ30 ቀበሌዎች ተስፋፍቶ ቀጥሏል ብለዋል።
የመከላከያ ሰራዊት ገብቷል ቢባልም አሁንም በአብዛኛው ቀበሌዎች ጥቃቱ እንዳለ በመግለጽ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።