በባስኬቶ እና መሎ ወረዳዎች መካከል የተጀመረው ግጭት ዛሬም አገርሽቶ ዋለ።

በባስኬቶ እና መሎ ወረዳዎች መካከል የተጀመረው ግጭት ዛሬም አገርሽቶ ዋለ።
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በሁለቱ ወረዳዎች ተወላጆች መካከል ትናንት ረቡዕ የተጀመረው ግጭት ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል። በግጭቱን እስካሁን ሶስት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡
ለረጅም ጊዜ ሁለቱ ማህበረሰቦች ለረጅም ጊዜ በፍቅር አብሮ ይኖር እንደነበሩ የሚገለጹት ነዋሪዎች፣ ኢህአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ ጀምሮ በዘር ፖለቲካ መታመስ መጀመራቸውንና የአሁኑ ግጭትም ከዚሁ ጋር እንደሚያያዝ ተናግረዋል።
አንዳንዶች የማሎ ወረዳ ነዋሪዎች ደግሞ “በመሎ ኮዛ ወረዳ የባስኬቶ ቋንቋ ተናጋሪ ናቸዉ በሚል ሰበብ የባስኬቶኛ ቋንቋ ተናጋሪዎቹ ሁለት ሆነዉ ሳለ በተጨማሪ 10 የመሎ ኮዛ ወረዳ ቀበሌያትን በማስገደድ ወደ ባስኬቶ አድርጎ ለመውሰድና ዞን ለመሆን በማሰብ የተፈጠረ ችግር ነው በማለት ይገልጻሉ። ባስኬቶ ልዩ ወረዳ በራሱ ዞን መሆን ሲችል በማሎ ወረዳ ስር የሚተዳደሩትን ቀበሌዎች ሊነካ አይገባም በማለት የማሎ ወረዳ ነዋሪዎች ይቃወማሉ።
በአካባቢው የራሳቸውን ስልጣን ለማስቀጠል በመፈለግ ሁለቱን ማህበረሰቦች ለማጋጨት ደፋ ቀና የሚሉ ባለስልጣናት መኖራቸውንም ነዋሪዎች ይናገራሉ።