በባህርዳር የስራ ማቆም አድማው በጉልበት ለማስቆም የሚወሰደው እርምጃ ቀጥሎአል

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ላለፉት ሁለት ቀናት በተሳካ ሁኔታ የተካሄደውን የስራ ማቆም አድማ ለማስቀረት ገዢው ፓርቲ እየወሰደ ባለው እርምጃ ከ20 በላይ ነጋዴዎች የታሰሩ ሲሆን፣ የተወሰኑ ሱቆችም በግዳጅ ድርጅታቸውን እንዲከፈቱ ተደርጓል።

በከተማው የሚካሄደውን  አድማ ለማስቆም ገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ጫና በማድረግ ላይ ቢሆንም፣ የመጣው ይምጣ በሚል በድፍረት አሁንም አድማውን ተግባራዊ እያደረጉ ያሉ ድርጅቶች በርካታ ናቸው።