በባህርዳር ከተማ በሙስሊሞች እና በፖሊስ መካከል ግጭት ተፈጠረ

ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህር ዳር ከተማ በህዝበ ሙስሊሙ መካነ መቃብር አጠገብ የሚገኘውን ትንሽ ቦታ መንግስት ሞይንኮ ለተሰኘ  የመኪና ጋራጅ  ድርጅት አሳልፎ መስጠቱን ተከትሎ የአካባቢው ሙስሊም ባነሳው ተቃውሞ ምክንያት  ድርጅቱ ቦታውን እንደማይወስድ እና እንደማይረከብ አስታውቆ ነበር።
ትናንት ህዝበ ሙስሊሙ ቦታውን ለማጠር እና አታክልት ለመትከል ሲሰባሰብ የፌደራል ፖሊስ በፍጥነት በመምጣት ያስቆማቸው ሲሆን እርምጃውን ተከትሎ በሙስሊሙ ማህበረሰብ እና በፌደራሎቹ መካከል ግጭት ተከስቱዋል፡፡

በተፈጠረው አለመግባበባትም ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሙስሊሞች የታሰሩ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ ባሰማው ተቃውሞ እና ትግልም ከታሰሩት መካከል የተወሰኑት ምሺት ላይ ተለቀዋል፡፡

ሼህ ሙሃመድ ታከለ እና አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ ሹፌር መታሰሩም ታውቋል።