(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2011)በቢሾፍቱ የተከሰተው የውሃ ችግር ለከፋ ችግር ዳርጎናል ሲሉ ነዋሪዎቹ ለኢሳት ገለጹ።
በተለያዩ ቀበሌዎች ተከሰተ የተባለው የውሃ ችግር አንድ ወር እንዳለፈውም ነዋሪዎቹ ይገልጻሉ።
እነሱ እንደሚሉት ከሆነ የውሃ መጥፋቱ ብቻ ሳይሆን ውሃ ያለበትን አካባቢ ፈልጎ ማግኘትና ለውሃ መጫኛና መቅጃ የሚያወጡት ወጪ እንዳማረራቸውም ይናገራሉ።
ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል አቤት ማለታቸውንና ከሚመለከተው አካል በትዕግስት ጠብቁ ከሚባለው ምላሽ ውጪ ምንም መፍትሄ አለመገኘቱንም ይናገራሉ።
ኢሳትም ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ከተማዋ ውሃ ቢሮ ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢያደርግም ምላሽ ግን ማግኘት አልቻለም።