በቢልዮን የሚገመት ብር የወጣባቸው የውሃ ተቋማት ደረቁ

ግንቦት ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለክልሉ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት 1 ቢሊዮን 900 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረጋባቸው 102 ጥልቅ የመጠጥ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮዎች ግንባታቸው ተከናውኖ ውሃ መሰጠት በጀመሩ በወራት እና በሳምንታት ውስጥ መድረቃቸውን ገልጸዋል።
በዚህም የተነሳ በክልሉ የነበረው የመጠጥ ውሃ ሽፋን በገጠር ከ72 በመቶ በታች ሆኗል ብለዋል።