ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያአዘ በቅርቡ በጋሞጎፋ ዞን በቁቻ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት በርካታ ሰዎች መካከል 13ቱ ዛሬ በዋስ የተለቀቁ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ደግሞ ለሀምሌ 25 መቀጠራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
በቅርቡ በወረዳው የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የከተማዋ አገር ሽማግሌዎች እና ታዋቂ ሰዎች መታሰራቸው ይታወቃል ።