በቁጫ ወረዳ ታስረው የነበሩ ሰዎች ተለቀቁ

መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በቁጫ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ታስረው የነበሩ 40 ሰዎች ተፈቱ። አስተባባሪ ናቸው በሚል የታሰሩት መቶ አለቃ ማሴቦ ማዳልጮ ግን ሳይፈቱ ቀርተዋል።

ሰዎቹ ከ3 ወራት በፊት ፍርድ ቤት እንዲፈቱ ውሳኔ ቢያስተላልፍም ፖሊስ በራሱ ስልጣን አልፈታም ብሎ መቆየቱን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል። ይሁን እንጅ እስረኞቹ በትናንትው እለት ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክታል።

ቁጫ ወረዳ ናዋሪዎች ከማንነት ጋር በተያያዘ ከመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተው እንደነበር ይታወቃል።