ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነትና ከአስተዳደር መብት ጋር በተያያዘ ለአመታት የዘለቀው የቁጫ ህዝብ ጥያቄ፣ ምላሽ ባላገኘበት ሁኔታ፣ አሁንም የሚታሰሩ ሰዎች መኖራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
ከ140 በላይ የአካባቢው የአገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ካለፉት ሁለት አመታ ጀምሮ በእስር ላይ ናቸው። ይሁን እንጅ ሰሞኑን ሌሎች የመንግስት ሰራተኞችም መታሰራቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት ገልጸዋል።
በአካባቢው የሚታየው አፈና ከአቅም በላይ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ለጥያቄው መልስ የሚሰጥ አካል ቢጠፋም፣ ትግሉ ግን በተለያዩ መንገዶች እየተካሄደ መሆኑን ይናገራሉ።