ታኀሳስ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ሰዎች እንደገለጹት በአፋርና በኢሳ መካካል ያለውን የቆየ የድንበር ውዝግብ ተከትሎ መንግስት የተወሰኑ ቦታዎች ወደ አፋር ክልል እንዲካተቱ መወሰኑን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ 7 ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች ሲገደሉ ከ30 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል። በርካታ ሰዎችም ተይዘው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል።
አሁንም በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት የሰፈነ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስትን የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎችንም እያደረጉ ነው። በጉዳዩ ዙሪያ የአካባቢውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።