በሽንሌ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ሲካሄድ በሞያሌ እንደገና ግጭት ተነሳ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮ ሶማሊ ክልል በሺንሌ ዞን ዛሬ ሲካሄድ በዋለው ተቃውሞ ህዝቡ የወረዳ አስተዳዳሪዎችን ከከተማ ከማባረሩ በተጨማሪ እስር ቤት ሰብሮ በመግባት እስረኞችን አስፈትቷል። ኤረር ውስጥ የአብዲ ኢሌ የእህት ልጅ የሆነው የወረዳው አስተዳዳሪ የአቶ ሃሰን አብዲ ኢሌ መኖሪያ ግቢ ተሰባብሯል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ የሽንሌ ህዝብ ተቃውሞውን እንዲያቆም ሲማጸኑ ውለዋል።
አመራሮች፣በሽንሌ ዞን ከፍተኛ የሆነ ሙስና ፣ አስገድዶ መድፈርና ሰቆቃወ ሲፈጸሙ መቆየታቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
በሞያሌ በድጋሜ በተነሳው ተቃውሞ ደግሞ የፖሊስ ጽ/ቤቱ መቃጠሉ ታውቋል።