በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች አዋሽ ውስጥ ታስረዋል

ነሃሴ  ፲፮ ( አሥራ  ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነሃሴ 6 ቀን 2008 ዓም በአዲስ አበባ ተካሄዶ በነበረው ተቃውሞ የተያዙ ከ2500 በላይ ዜጎች አዋሽ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው። ታስረው ከተፈቱት መካከል አንዳንዶች እንደገለጹት ውሃ ውስጥ እንዲገቡ እየተደረጉ ተደብድበዋል። በጠጠር እና በእሾህ ላይ እንዲሮጡ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ከ2 ሺ 400 በላይ እስረኞች አሁንም በእስር ቤቱ ውስጥ ይገኛሉ።

በአዳማ ደግሞ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ700 በላይ ወጣቶች አዳማ በሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ታስረው፣ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው። ቤተሰቦቻቸው እንዳይጎበኙዋቸው መደረጉንና በየቀኑ ከፍተኛ ድብደባ እንደሚፈጸምባቸው ምንጮች ገልጸዋል።