በሶሪያ ግጭት ከ100 ሺ በላይ ሰዎች ተገደሉ

ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ እንደገለጹት በሶሪያ የበሽር አላሳድን መንግስት ለመገልበጥ የተቃውሞ ትግል ከተጀመረበት ካለፉት 3 አመታት  ጀምሮ ከ100 ሺ ህዝብ በላይ ተገድላል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ባለፈው ወር ካወጣው አሀዝ ጋር ሲነጻጸር የማቾች ቁጥር በ7 ሺ ከፍ ብሎአል።

ባንኪሙን ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ጆን ኬሪ ጋር በመሆን ነው መግለጫውን የሰጡት። ሁለቱም ወገኖች ለሶሪያ ችግር የፖለቲካ መፍትሄ እንዲገኝ አሳስበዋል።