በሶማሊ ክልል የካቢኔ አባላት መካከል ያለው ፍጥቻ እንደቀጠለ ነው

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በክልሉ ፕሬዚዳንት አብዲ ኢሌ ፣ በሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሲያ ፓርተ (ሶህዴፓ) ሊቀመንበርና ከፕሬዚዳንቱ

ጎሳ የሆኑ በአንድ ወገን፣ 3 ምክትል ፕሬዚዳንቶችና የ4 ካቢኔ አባላት በሌላ በኩል ሆነው የጀመሩት እሰጥ አገባ ጠ/ሚኒስትሩ ጋር ደርሶና በድርጅት ደረጃ

ግምገማ አድርገው መፍትሄ እንዲሰጡት ስምምነት ከተደረሰ በሁዋላ፣ ፕሬዚዳንቱ ግምገማውን ለማደናቀፍ በዛሬው እለት ከጄኔራል አብርሃ ጋር ለአስቸኳይ

የደህንነት ስብሰባ ተቀምጠዋል። ጄኔራል አብርሃ ትናንት ጅጅጋ የገቡ ሲሆን አመጣጣቸውም በአንደኛው ወገን የተጀመረውን ስብሰባ ለማስቆም ነው።

ሰሞኑን በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት በተደረገው ግመገማ አቶ አብዲ ሰሩዋቸው የተባሉ በርካታ ወንጀሎች ተዘርዝረው ቀርበዋል። አቶ ሃይለማርያም አስቸኳይ

እርምጃ እንደሚወሰድ ቢዝቱም፣ የጄ/ል አብርሃምን ተጽእኖ ተቋቁመው አቶ አብዲን ከስልጣን ላያስነሱዋቸው ይችላሉ በማለት ተዛቢዎች ይናገራሉ።

በጄ/ል አብርሃና በአቶ አብዲ መካከል  ከፍተኛ የሆነ የጥቅም ትስስር መኖሩ መዘገቡ ይታወቃል፡